Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dhs

DHS

 

In observance of “Second Chance Month”, the DHS READY Center team is hosting a FAMM Foundation production screening of the documentary “District of Second Chances”. Learn more

The DHS ERAP application portal is open and accepting applications. The portal will remain open until 8,500 applications are receivedLearn more
 

Want to help? Here is how. Learn more

 

There is a Temporary Local Benefit to households receiving the Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP) for the period January 1, 2024, through September 30, 2024. Learn more

 

List Your Units Here Today! Read more
 

 

 

የDHS መረጃ - Amharic (አማርኛ)

ይህ ድረገጽ የዲሲ ሰብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ የሚመለከት ጠቃሚ መረጃ ይዟል። ይህን መረጃ ለመረዳት በቋንቋዎ እርዳታ ከፈለጉ፣ DHS ነጻ የቋንቋ ትርጉም አገልግሎቶችን ያቀርባል። እነዚህን አገልግሎቶች ለማግኘት፣ እባክዎ በ 202-671-4200 ይደውሉ።

የኤጀንሲ ስም፥ Department of Human Services (የሰብአዊ አገልግሎቶች መምሪያ)

ስለ DHS

የዲሲ ብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ ተልዕኮ ትርጉም ያላቸው የስራ እድሎች ግንኙነቶችን፣ የኢኮኖሚ እርዳታ፣ እና የድጋፍ አገልግሎቶችን በማቅረብ እያንዳቸው የዲስትሪክት ኗሪዎች ሙሉ አቅማቸው እንዲደርሱ ማጎልበት ነው።

ጥቅሞች

Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP) (ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም)

የዲስትሪክቱ ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም (SNAP) (በፊት የምግብ ማህተም ተብሎ ይታወቃል) ለተገዛ ምግብ ወርሃዊ ጥቅማጥቅሞችን በማቅረብ ዝቅተኛ-ገቢ ያላቸው ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን ያግዛል። SNAP ጥቅማጥቅሞች በኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅሞች ማስተላለፊያ (EBT) ካርድ፣ እንደ ብድር ካርድ የሚጠቅም፣ ላይ ይቀርባሉ። EBT ካርዶች በብዙ የግሮሰሪ መደብሮች፣ የተወሰኑ የግብርና ምርቶች ገበያ (ፋርመርስ ማርኬት)፣ መስማማት፣ የትልቁ ሳጥን (ቢግ ቦክስ) መደብሮች፣ እና የተወሰኑ የኢንተርኔት ላይ መደብሮች ይቀበላሉ። የSNAP ጥቅማጥቅሞች በአጠቃላይ የተዘጋጁ ምግቦችን፣ ቫይታምኖች፣ አልኮል/ሲጃራ፣ እና ምግብ ያልሆኑ ዓይነቶችን (እንደ ሰሙና ወይም የጥርስ ሰሙና አይነት) ለመግዛት መጥቀም አይችሉም።

ማመልከቻ በመሞላት፣ ብቁነትዎን ለማረጋገጥ ሰነዶችን በማቅረብ፣ እና ቃለ-መጠይቅ ውስጥ በመሳተፍ ለSNAP ማመልከት ይችላሉ። ማመልከቻዎች በኢንተርኔት፣ ሞባይል መተግበሪያ፣ በ-አካል፣ ፋክስ (202-671-4400)፣ ወይም በፖስታአማካኝነት ይቀበላሉ።

ስለ ብቁነት መስፈርቶች፣ ሂደት ላይ ያለው ብቁነት፣ የስራ ቅጥር እና የስልጠና አገልግሎቶች ለ SNAP ተቀባዮች የበለጠ ለማወቅ፣ እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ላይ እዚህይጫኑ። ብቁሊሆኑ እንደሚችሉ ካሰቡ – እንዲያመለክቱ እናበረታታዎታለን።

TANF ለዲስትሪክት ቤተሰቦች

የዲስትሪክቱ ጊዜያዊ እርዳታ ለተቸገሩ ቤተሰቦች (TANF) ፕሮግራም የተቸገሩ ቤተሰቦች ወደ ስኬት ጎዳና እንዲሄዱ ለማመቻቸት የጥሬ ገንዘብ እርዳታን ከተከታታይ አገልግሎቶች ጋር ይሰጣቸዋል። በዲስትሪክቱ የTANF ፕሮግራም ውስጥ የተመዘገቡ ቤተሰቦች የገቢ ብቁነት እስካላቸው እና በቤቱ ውስጥ ልጅ እስካላቸው ድረስ ጥቅማጥቅሞችን ሊቀበሉ ይችላሉ። እንዲሁም፣ TANF የግለሰባቸውን ፍላጎቶች ለማሟላት አንድ ላይ መጠቅለል የሚችሏቸው የተለያዩ የድጋፍ አገልግሎቶችን ያቀርባሉ። ልጆች እና ወላጆች አንድ ላይ መነሳት እንድችሉ ቤተሰቦችን ለማገልገል እና ተደራሽነትን ለመፍጠር DHS የሁለት-ትውልድ ዘዴን ይተገብራል።

ማመልከቻ በመሞላት፣ ብቁነትዎን ለማረጋገጥ ሰነዶችን በማቅረብ፣ እና ቃለ-መጠይቅ ውስጥ በመሳተፍ ለSNAP ማመልከት ይችላሉ። ማመልከቻዎች በኢንተርኔት፣ ሞባይል መተግበሪያ፣ በ-አካል፣ ወይም በፖስታአማካኝነት ይቀበላሉ።

ስለ ብቁነት መስፈርቶች፣ የስራ መስፈርቶች፣ የገቢ ገደቦች፣ ወርሃዊ የTANF ጥቅማጥቅም መጠን፣በሂደት ላይ ያለው ብቁነት፣ የስራ ቅጥር እና የስልጠና አገልግሎቶች ለ SNAP ተቀባዮች የበለጠ ለማወቅ፣ እና እንዴት ማመልከት እንደሚቻል ላይ እዚህይጫኑ። ብቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ ካሰቡ – እንዲያመለክቱ እናበረታታዎታለን።

የህክምና እርዳታ

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የገቢ-ብቁነት ላላቸው ኗሪዎች በMedicaid (ሜዲኬይድ)፣ Alliance (አሊያንስ)፣ እና DC Healthy Families (የዲሲ ጤናማ ቤተሰቦች) ፕሮግራሞች አማካኝነት የህክምና ሽፋንን ያቀርባል። እንዲሁም DHS ባለፉት 3 ወራት ውስጥ የህክምና ወጪ ክፍያዎችን (የሬትሮ Medicaid) በመክፈል ውስጥ ያግዛል።

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት Medicaid የጤና እንክብካቤ ሽፋንን ዝቅተኛ-ገቢ ላላቸው እና/ወይም አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ግለሰቦች እና ቤተሰቦች የሚያቀርብ የፌዴራል/ስቴት የጋራ የጤና መድን ነው። Medicaid ብዙ አገልግሎቶችን ይሸፍናል፣ የሀኪም ጉብኝቶች፣ የሆስፒታል እንክብካቤ፣ የትዕዛዝ መድሃኒቶችን፣ የአዕምሮ ጤና አገልግሎቶችን፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ብዙ አገልግሎቶችን ጨምሮ። በዲስትሪክቱ ውስጥ ለMedicaid ብቁ ለመሆን፣ አመልካቾች የዲስትሪክቱ ኗሪዎች መሆን እና የገንዘብና የገንዘብ-ያልሆኑ መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። ባሁን ጊዜ፣ ከ3 የዲስትሪክት ኗሪዎች 1 በMedicaid ፕሮግራም አማካኝነት ጥራት ያለው የጤና እንክብካቤን ይቀበላል።

የዲሲ የጤና እንክብካቤ ትብብር ፕሮግራም (“ዘ አሊያንስ”) is ለ Medicaid ብቁ ላልሆኑ የዲስትሪክት ኗሪዎች የህክምና እርዳታን ለማቅረብ የተቀረጸ በአካባቢ-መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት ፕሮግራም ነው። የአሊያንስ ፕሮግራም ሌላ የጤና መድን የሌላቸው እና ለMedicaid ወይም Medicare ብቁ ያልሆኑ ዝቅተኛ-ገቢ ያላቸው የዲስትሪክት ፕሮግራሞችን ያገለግላል።

የዲሲ ጤናማ ቤተሰቦች ለMedicaid ብቁ ለመሆን የተወሰኑ የገቢ እና የU.S. ዜግነት ወይም ብቁ የኢሚግሬሽን ሁኔታ መስፍርቶችን ለሚያሟሉ የዲሲ ኗሪዎች ነጻ የጤና መድን የሚያቀርብ ፕሮግራም ነው። የዲሲ ጤናማ ቤተሰቦች ፕሮግራም የሀኪም ጉብኝቶችን፣ የዓይን እና የጥርስ እንክብካቤ፣ የትዕዛዝ መድሃኒቶች፣ የሆስፒታል ቆይታዎች፣ እና ለቀጠሮዎች የትራንስፖርት አገልግሎትን ይሸፍናል። እንዲሁም የዲሲ ጤናማ ቤተሰቦች አዲስ ለተወለዱ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኛ የሆኑ ወይም ልዩ የጤና እንክብካቤ ፍላጎቶች ላላቸው ልጆች፣ እና HIV (ኤች አይ ቪ) እና AIDS (ኤይድስ) ላለባቸው ሰዎች ልዩ ፕሮግራሞችን ያቀርባል።

የሬትሮ ሜዲኬይድ (Retro Medicaid) የባለፉት 3 ወራት የህክምና ወጪ ክፍያዎችን ለመክፈል እርዳታ ለሚፈልጉ ሰዎች ነው። እርስዎ እና/ወይም የቤተሰብ አባል ለ ወደኋላ-ተመላሽ ሜዲኬይድ (Retroactive Medicaid) ሽፋን ብቁ ለመሆን፣ በ ወደኋላ-ተመላሽ ጊዜ ወቅት ሁሉም የMedicaid የብቁነት መስፈርቶችን ማሟላት አለባችሁ።

አሁን ለህክምና እርዳታ ብቁ ለመሆን አራት መንገዶች አሉ

  1. በኢንተርኔት (በጣም ፈጣኑ መንገድ)
  2. ሞባይል መተግበርያ
  3. በ 1 (855) 532-5465 ይደውሉ እና በስልክ ያመልክቱ
  4. የወረቀት ማመልከቻ (ፖስታ፣ ኢሜይል፣ በ-አካል፣ ወይም ፋክስ)
    • የተፈረመ ማመልከቻዎችን ወደሚከተለው የፖስታ አድራሻ ይላኩ፥
      የሰብዓዊ አገልግሎቶች መምርያ | የኢኮኖሚያዊ ደህንነት አስተዳደር
      P.O. Box 91560 Washington, DC 20090
      የጉዳይ መዝገብ መቆጣጠሪያ ክፍል


      ማመልከቻውን ወደ (202) 671-4400 ፋክስ ያድርጉ


      ማመልከቻውን በአቅራቢያዎ ወዳለው የአገልግሎት ማእከል በአካል ይመልሱ፣ከ 7:30 ጧት እስከ 4:45 ከሰዓት፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ።

የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች

የሚደጎም የልጅ እንክብካቤ ፕሮግራም ለገቢ-ብቁ የሆኑ ቤተሰቦች የልጅ እንክብካቤ ክፍያዎቻቸውን እንዲከፍሉ ይረዳል። የልጅ እንክብካቤ ድጎማ የፍላጎት፣ ገቢ፣ እና ቤተሰብ መጠን ግምገማ ላይ የተመሰረተ ነው። ለእርዳታ ለማመልከት፣ ወላጆች የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች ክፍልን መጎብኘት አለባቸው። የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች ክፍል በሮች በ 7:30 ጧት ይከፈታሉ እና በ 4:45 ከሰዓት ይዘጋሉ። ጎብኚዎች ለቀጠሮዎች ቀድመው እንዲደርሱ ይበረታታሉ። ለአዲስ አመልካቾች የተገደቡ በእግር-መሄጃ ጉብኝቶች በ "መጀመሪያ-የመጣ፣ መጀመሪያ-ይገለገላል" መሰረት ይገኛሉ፥ ሰኞ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ፣ ከጧት 8:15 - 3:30 ከሰዓት።

የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች ክፍል (CCSD) በሚከተለው አድራሻ ይገኛል፥

Congress Heights (ኮንግረስ ሄይትስ)
የአገልግሎት ማእከል 4049 South Capitol (ሳውዝ ካፒቶል) መንገድ፣
SW Washington (ደቡብ ምእራብ ዋሺንግተን)፣ DC (ዲሲ) 20032
የልጅ እንክብካቤ ድጎማ መግቢያ ቅጾች በ [email protected] ይላካሉ

የቀብር ድጋፍ

የቀብር ድጋፍ መርሀግብር የቀብር ስነ ስርዓት ወጪን እስከ የመጨረሻ $1,000.00 ወይም ለሚቃጠል በድን ደግሞ $650.00 ድጋፍ ያሰጣል። የሞተው ሰው መስፈርቱን ያሟላል ተብሎ ከታማነበት ድጋፍ ይሰጣል እና የቀብር ስነስርዓት ወይም በድን ማቃጠያ ጠቅላላ ወጪው ከ$2,000.00 ወጪ በላይ አይበልጥም ከመጠን በላይ ግዙፍ ሬሳ ሳጥን የሚያስፈልገው አንድ ሕይወቱ ያለፈ ግለሰብ ጠቅላላ የቀብር ስነ ስርዓት ወጪው ከ $3,000.00 በላይ መብለጥ አየለብትም። የቀብር ስነስርዓት ድጋፍ ክፍያዎች የሚሰጠው የሞተው ግለሰብ የቅርብ ዘመድ በመረጠው ኮንትራት ውስጥ የገባው የቀብር ስነሰርዓት አስፈፃሚ ጋር ድርጀት ነው። ማመልከት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እዚህይጫኑ።

ጊዚያዊ የአካል ጉድለት እርዳታ

ጊዚያዊ የአካል ጉድለት እርዳታ (IDA) ፕሮግራም በአካል ጉዳተኝነት ምክንያት መስራት ለማይችሉ እና የፌዴራል ተጨማሪ የዋስትና ገቢ(SSI) ለመቀበል ከፍተኛ እድል ላላቸው ጊዜያዊ የገንዘብ እርዳታን ያቀርባል። የIDA ክፍያዎች የ SSI ብቁነት እስከሚጸድቅ ወይም እስከሚከለከል ድረስ ይወጣሉ። ማመልከት ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት፣ እዚህይጫኑ።

እንዴት ማመልከት እንደሚቻል፥

የመጀመሪያ ማመልከቻ ማስገባት ይችላሉ (ሁሉም ፕሮግራሞች) ወይም የዳግም-ማረጋገጫ/እድሳት መሙላት (ሁሉም ፕሮግራሞች)፣ ወይም የSNAP የመካከለኛ-ማረጋገጫ ከሶስት መንገዶች በአንዱ ማስገባት፥

  1. ኦንላይን
    District Direct ድረገጽ ይጠቀሙ። የአገልግሎት ማእከልን ሳይገበኙ እና በመስመር ውስጥ ሳይጠብቁ ብቁ እንደሚሆኑ፣ ማመልከት እንደሚችሉ፣ ጥቅማጥቅሞችን እንደገና ማሳደስ፣ እና የSNAP -የመካከለኛ ማረጋገጫን መሙላት እንደሚችሉ ማየት ይችላሉ።

  2. ሞባይል ስልክ
    District Direct የሞባይል መተግበሪያንይጠቀሙ የአገልግሎት ማእከልን ሳይገበኙ እና በመስመር ውስጥ ሳይጠብቁ ብቁ እንደሚሆኑ፣ ማመልከት እንደሚችሉ፣ ጥቅማጥቅሞችን እንደገና ማሳደስ፣ እና የSNAP -የአጋማሽ ማረጋገጫን መሙላት እንደሚችሉ ማየት ይችላሉ። መተግበሪያው ለአይፎን (IOS) በ አፕል አፕ ስቶር ወይም ለአንድሮይድ መሳሪያዎች ከሆነ በጉግል ፕሌይ ስቶር ይገኛል።

  3. የወረቀት ማመልከቻዎች (ፖስታ፣ በአካል፣ ወይም ፋክስ)
    ትክክለኛውን የወረቀት ወይም ቅጽ ከታች ካለው ዝርዝር ያውርዱ፥

የተነቀናጀ ማመልከቻ ለህዝብ እርዳታ ጥቅማጥቅሞች (ለህክምና እርዳታ፣ SNAP፣ TANF፣ እና የገንዘብ እርዳታ)
ኢንግሊዝኛ ስፓንኛ አማርኛፈረንሳይኛ የተቃለለ ቻይንኛ

SNAP፣ TANF፣ እና የገንዘብ እርዳታ ዳግም-ማረጋገጫ
ኢንግሊዝኛ ስፓንኛ አማርኛፈረንሳይኛ የተቃለለ ቻይንኛ

የSNAP የአጋማሽ-ማረጋገጫ
ኢንግሊዝኛ ስፓንኛ አማርኛ

ወደኋላ-ተመላሽ የMedicaid ሽፋን
ኢንግሊዝኛ ስፓንኛ

የአሊያንስ እና ስድተኛ ህጻናት ፕሮግራም እድሳት – 1209
ኢንግሊዝኛ ስፓንኛ አማርኛፈረንሳይኛ የተቃለለ ቻይንኛ

የቀብር እርዳታ ማመልከቻ
ኢንግሊዝኛ ስፓንኛ አማርኛ

ማመልከቻውን በፖስታ መላክ ይችላሉ፣ ወደ፥
ሰብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ | የኢኮኖሚ ዋስትና አስተዳደር የጉዳይ መዝገብ መቆጣጠሪያ ክፍል
P.O. Box 91560
Washington, DC 20090

ማመልከቻውን ፋክስ ማድረግ ይችላሉ፣ ወደ (202) 671-4400

ማመልከቻ/ቅጽ ሄዱ ለማስቀመጥ ወይም ለመውሰድ በአቅራቢያዎ ያለውን የአገልግሎት ማእከል ያግኙ።

በአቅራቢያዎ ያለውን የአገልግሎት ማእከል ያግኙ

የአገልግሎት ማእከል

አድራሻ

የአሰራር

ሁኔታ

Anacostia

2100 Marthin Luther King Jr. Avenue, SE

ክፍት ነው

FORT DAVIS*

3851 Alabama Avenue, SE

ተዘግቷል

CONGRESS HEIGHTS

4049 South Capitol Street, SW

ክፍት ነው

H STREET**

645 H Street, NE***

ክፍት ነው

TAYLOR STREET*

1207 Taylor Street, NW

ተዘግቷል

*የቴይለር ስትሪት እና የፎርት ዴቪስ የአገልግሎት ማእከላት ለጊዜው ዝግ ነው።
**ጊዜያዊ የአካል ጉዳተኝነት እርዳታ ማመልከቻዎች በ 645 H Street NE በሚገኘው የኤች ስትሪት አገልግሎት ማእከል፣ በኢንተርኔት፣ ወይም በ District Direct የሞባይል ማመልከቻ አማካኝነት ይቀበላሉ።

ማስታወሻ፥ በአድራሻዎ አገልግሎት የሚሰጥ ማእከል የሚመለከት ጥያቄ ካለዎት፣ በ (202) 727-5355 ይደውሉ።

የቋንቋ እምባ ጠባቂ የግንኙነት አድራሻዎች እና መገኛ ቦታዎች

እያንዳንዱ የሰብዓዊ አገልግሎቶች መምሪያ (DHS) የኢኮኖሚ ዋስትና አስተዳደር (ESA) የአገልግሎት ማእከል (የአገልግሎት ማእከል) በቋንቋ ተግዳሮት ምክንያት የDHS አገልግሎቶችን ለማግኘት ችግሮች የሚያጋጥሙትን ማንኛውንም የተገደበ የኢንግሊዝኛ ችሎታ ወይም ኢንግሊዝኛ-ችሎታ የሌለው (LEP/NEP) ደንበኛን ለማገዝ የተቀመጠ፣ እምባ ጠባቂ ተብሎ የሚጠራውን፣ መድቧል።

የአገልግሎት ማእከል

ስፍራ

ቀዳሚ

እምባ ጠባቂ

አማራጭ

እምባ ጠባቂ

Anacostia

2100 Martin Luther King Avenue, SE

(202) 841-1508

(202) 304-7525

Congress Heights

4049 South Capitol St. SW

(202) 645-4576

(202) 645-4534

Ft. Davis

3851 Alabama Ave. SE.

(202) 841-4063

(202) 841-0158

H Street Service

Center - ዋና

645 H Street, NE

(202) 821-3294

(202) 394-1788

Taylor Street

1207 Taylor Street, NW

(202) 531-1048

(202) 531-1541

የMedicaid ቅርንጫፍ

645 H Street, NE

(202) 698-4168

(202) 702-9712

ማዕከላዊ ማቀነባበሪያ ክፍል

645 H Street, NE

(202) 842-0668

(202) 727-9944

የቤት አልባ አገልግሎቶች

የኛ ራዕይ ቤት አልባነት በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ውስጥ ያልተለመደ፣ ለአጭር ጊዜ የሚቆይ፣ እና ደጋግሞ የማያጋጥም እንዲሆን ነው። በቤት አልባ አገልግሎት ሲስተም ውስጥ ዘርን መሰረት ያደረገ ኢፍትሃዊነትን አስወግደን ሁሉም ሰዎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የሚስተናገዱበት ስርዓትን እንዘረጋለን።

ቤት አልባነት ላጋጠማቸው ቤተሰቦች አገልግሎቶች

ቤተሰብዎ ወይም የሚያውቁት ቤተሰብ በራሳቸው ሊፈቱት የማይችሉ የመኖሪያ ቤት ችግር እያጋጠማቸው ከሆነ፣ እባክዎ Virginia Williams Family Resource Center (ቨርጂኒያ ዊሊያምስ የቤተሰብ ግብዓት ማዕከል)(VWFRC)ን ያግኙ። የመጠለያው የስልክ መስመር በየቀኑ ከ 8 ጥዋት - 12 ጥዋት ክፍት ነው። በሃይፖተርሚያ (ዝቅተኛ የሰውነት ሙቀት) ወቅት (ኖቬምበር 1 - ኤፕሪል 15)፣ የመጠለያው የስልክ መስመር በቀን ለ24 ሰዓት ክፍት ነው።

በ VWFRC አማካኝነት የቤተሰብ የቤት አልባ አገልግሎቶች ብቁ ለመሆን፣ የዲስትሪክት ኗሪ መሆን አለብዎ፣ የሚያስተዳድሯቸው አካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች ወይም ጥገኛ የሆኑ አዋቂ ሰዎች ሊኖርዎ ይገባል፣ ወይም ነፍሰጡር እና በሶስተኛው ትራይምስተር መሆን አለብዎ፤ እና መቆየት የሚችሉበት ደህንነቱ የተጠበቅ ቦታ የሌሎት ሊሆኑ ይገባል። ከታች ያሉትን አገልግሎቶች ለማግኘት፣ በ VWFRC ሊገመገሙ እና ሪፈር ሊደረጉ ይገባል።

ቤት አልባነትን መከላከል

ዲስትሪክቱ ቤት አልባ የመሆን ስጋት ያለባቸው ቤተሰቦች እዚያው ማህበረሰብ ውስጥ ሆነው ቤተሰባቸውን ማረጋጋት የሚችሉበት አገልግሎቶችን እና ግብዓቶችን በመስጠት የመጠለያ ሲስተም ውስጥ እንዳይገቡ የሚከላከል ፕሮግራሞች አለው። ይህም ቤት አልባነት የመከላከል ፕሮግራም (HPP)፣ የድንገተኛ ጊዜ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እርዳታ፣ እና DC Flex ን ያካትታል።

ስለ ድንገተኛ ጊዜ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እርዳታ ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሎት፣ እባክዎ [email protected]ያግኙ።

የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ ለቤተሰቦች

ከአገልግሎት አቅራቢዎች ጋር በሚደረግ ውል፣ DHS ዓመቱን በሙሉ ቤት አልባነት ላጋጠማቸው ቤተሰቦች ደህንነታቸው በተጠበቀ እና በተከበሩ ህንጻዎች ውስጥ የድንገተኛ ጊዜ መጠለያዎችን ይሰጣል። እያንዳንዱ ፕሮግራም ሰፊ ማዕቀፍ ያለው ድጋፎችን እና የአገልግሎት ግንኙነቶችን ያቀርባል - ይህም ቤተሰቦች በ90 ቀናት ውስጥ የተረጋጋ መኖሪያ ቤት እንዲኖራቸው ሊያግዙ የሚችሉ – የመኖሪያ ቤት ፍለጋ፣ የአእምሮ ጤና እና የሥራ ስምሪት አገልግሎቶችን፣ እና ትርጉም ያለው የልጆች እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። የDHS የአደጋ ጊዜ መጠለያ ክፍሎች ዝርዝር የአፓርትመንት ዓይነት ክፍሎች እና የግል ክፍሎችን ሁለቱንም የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም የአጭር ጊዜ የቤተሰብ መኖሪያ ተብሎ ይታወቃል። ወደ የቤተሰብ መጠለያዎች የሚደረጉት ሁሉም ሪፈራሎች የሚደረጉት በ Virginia Williams Family Resource Center(ቨርጂኒያ ዊሊያምስ ፋምሊ ሪሶርስ ሴንተር) አማካኝነት ነው።

ለተጨማሪ ጥያቄዎች እና ስጋቶች፣ እባክዎ [email protected]ያግኙ።

የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች

DHS ቤት አልባነት ላጋጠማቸው ወይም ቤት አልባ የመሆን ስጋት ላለባቸው የዲስትሪክቱ ቤተሰቦች የመሸጋገሪያ እና ቋሚ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞችን ያቀርባል። እነዚህ ፕሮግራሞች የቤተሰብ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት የማረጋጊያ ፕሮግራም፣ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ለተለዩ ሰዎች፣ እና ቋሚ የመኖሪያ ቤት ድጋፍን ያካትታሉ። ወደነዚህ ፕሮግራሞች ሁሉም ሪፈራሎች የሚደረጉት በተቀናጀ የምዘና እና የመኖሪያ ቤት ምደባ (CAHP) ሲስተም አማካኝነት ነው። CAHP ቤት አልባነት ያጋጠማቸው ሰዎች በተቀናጀ የሪፈራል እና የመኖሪያ ቤት ምደባ ሂደት በአፋጣኝ እና የረጅም ጊዜ የመኖሪያ ቤት እና የአገልግሎት ፍላጎቶች በሁለቱም አማካኝነት ተገቢ የሆነ እርዳታ ማግኘታቸውን የሚያረጋገጥ የሁሉም ቤተሰቦች ተደራሽነት እና ምዘናን የሚወክል መደበኛ ስርዓት ነው። መላው የተቀናጀ የመግቢያ ሂደት፣ ከመጀመሪያው ተሳትፎ አንስቶ የተሳካ የመኖሪያ ቤት ምደባን እስኪያደርግ ድረስ በመደበኛ ሂደቱ ላይ "የተሳሳተ በር የለም" የሚለውን ዘዴ ይጠቀማል።

ስለ FRSP ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሎት፣ እባክዎ [email protected]ያግኙ

ቤት አልባነት ላጋጠማቸው ግለሰቦች አገልግሎቶች

እርስዎ ወይም የሚያውቋቸው ሌላ ሰው የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ ከፈለጉ፣ እባክዎ የመጠለያው የስልክ መስመር ጋር ይደውሉ በ (202) 399-7093 ወይም ወደ 311 ይደውሉ። የመጠለያው የስልክ መስመር በየቀኑ ከ 8 ጥዋት - 12 ጥዋት ክፍት ነው። በሃይፖተርሚያ (ዝቅተኛ የሰውነት ሙቀት) ወቅት (ኖቬምበር 1 - ኤፕሪል 15)፣ የመጠለያው የስልክ መስመር በቀን ለ24 ሰዓት ክፍት ነው። በሃይፖተርሚያ ወቅት ወደ መጠለያው የትራንስፖርት አገልግሎት 24 ሰዓት በቀን፣ 7 ቀናት በሳምንት ይገኛል።

ቤት አልባነት መከላከል እና ወደ መጠለያን ማስቀረት

ዲስትሪክቱ ቤት አልባ የመሆን ስጋት ያለባቸው ግለሰቦች የመጠለያ ሲስተሙ ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከል የሚያስችል፣ መጠለያን ማስቀረት የሚያስችል እና ፈጣን የመውጫ ፕሮግራሞች አለው። ይህ This Project Reconnect እና የድንገተኛ ጊዜ የኪራይ እርዳታን ያካትታል።

የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ

ቤት አልባነት ላጋጠማቸው አዋቂዎች የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ አለ። የድንገተኛ ጊዜ የመጠለያ ፕሮግራም ደህንነቱ የተጠበቀ የመኝታ ቦታ ለሌለው ማንኛውም ሰው፣ እንደአመጣጣቸው ቅደም ተከተል አልጋ ይሰጣል። መጠለያዎች ሞቃት እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሁም በስፍራው ላይ የምዘና እና የጉዳይ አስተዳደርን ማድረግ የሚቻልበትን የመኝታ ቦታን ይሰጣሉ። ፕሮግራሞች መጠለያ ለሚያገኙ ሰዎች በቦታው ላይ የተለያዩ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።

ዲስትሪክቱ በሃይፖተርሚያ ወቅት የአውትሪች ባለሞያዎችን እና የመጠለያውን ዓቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል እና በሃይፖተርሚያ ወቅት መጠለያው ተደራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ ተግቶ ይሰራል።

የመጠለያ የስልክ መስመር

የመጠለያው የስልክ መስመር በየቀኑ ከ 8 ጥዋት - 12 ጥዋት ክፍት ነው። በሃይፖተርሚያ (ዝቅተኛ የሰውነት ሙቀት) ወቅት (ኖቬምበር 1 - ኤፕሪል 15)፣ የመጠለያው የስልክ መስመር በቀን ለ24 ሰዓት ክፍት ነው። በሃይፖተርሚያ ወቅት ወደ መጠለያው የትራንስፖርት አገልግሎት 24 ሰዓት በቀን፣ 7 ቀናት በሳምንት ይገኛል። እርስዎ መጠለያ የሚያስፈልግዎ ከሆነ፣ ወይም መጠለያ ወይም የዌልፌር ቼክ የሚያስፈልገው ሰው ካዩ፣ የመጠለያው የስልክ መስመር ጋር በ (202) 399-7093 ወይም 311 ይደውሉ። አጣዳፊ የደህንነት ስጋት ካለ ወደ 911 ይደውሉ። በሚደውሉበት ጊዜ፣ እባክዎ ጊዜውን፣ የታዩበትን አድራሻ ወይም ቦታ፣ እና የግለሰቡን ገጽታ መግለጫ ያካትቱ።

የቀን እና የአውትሪች አገልግሎቶች

የዲስትሪክቱ የቀን ማዕከላት ቤት አልባነት ያጋጠማቸው ግለሰቦች የዕለት ተዕለት ፍላጎቶችን የሚያሟሉበት እና የረጅም ጊዜ አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን ማግኘት የሚችሉበት ደህንነቱ እና ክብሩ የተከበረ የቀን የመዋያ ቦታን ይሰጣል።

ኮምፕሬሄንሲቭ ስትሪት አውትሪች ኔትዎርክ ጎዳና ላይ ወይም ለሰው መኖሪያነት ብቁ ያልሆነ አካባቢ ለሚኖሩ ግለሰቦች ስልታዊ ድጋፍ ይሰጣል። ኔትዎርኩ መጠለያ የሌላቸው ብቻቸውን የሆኑ አዋቂ ሰዎችን በማሳተፍ የመጠለያ እና የመኖሪያ ቤት ድጋፎችን፣ የህዝብ ጥቅማጥቅሞች፣ የአካል እና የባህርይ ጤና እንክብካቤ፣ የጉዳት ቅነሳ ጣልቃገብነቶች፣ እና ሌሎች ግብዓቶችን ማግኘት የሚችሉበትን ግንኙነቶች የሚያስተባብር የጉዳይ አስተዳደር ያቀርባል።

የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች

DHS ቤት አልባነት ላጋጠማቸው ወይም ቤት አልባ የመሆን ስጋት ላለባቸው የዲስትሪክቱ ኗሪዎች የመሸጋገሪያ እና ቋሚ የመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞችን ያቀርባል። እነዚህ ፕሮግራሞች የቤተሰብ የመኖሪያ ቤት አቅርቦት የማረጋጊያ ፕሮግራም፣ ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት ለተለዩ ሰዎች፣ እና ቋሚ የመኖሪያ ቤት ድጋፍን ያካትታሉ። ወደነዚህ ፕሮግራሞች ሁሉም ሪፈራሎች የሚደረጉት በተቀናጀ የምዘና እና የመኖሪያ ቤት ምደባ (CAHP) ሲስተም አማካኝነት ነው።

ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎ [email protected] ያግኙ

የወጣቶች የቤት አልባ አገልግሎቶች

የDC የሰብዓዊ አገልግሎቶች ዲፓርትመንት (DHS) በወጣቶች የቤት አልባ አገልግሎቶች አማካኝነት ለሚከተሉት ፕሮግራሞች (በሌላ ሁኔታ ካልተገለጸ በስተቀር) የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል፣

የጎዳና አውትሪች

  • Friendship Place(ፍሬንድሺፕ ፕሌስ) - (202) 631-5008

Drop-In Centers(የማህበረሰብ ማዕከላት)

  • Sasha Bruce Youthwork(ሳሻ ብሩስ ዩዝ ኔትዎርክ)
    741 8th Street SE - (202) 675-9340 x214,215*
  • Latin American Youth Center (ላቲን አሜሪካን ዩዝ ሴንተር)(LAYC)
    3045 15 Street NW - (202) 713-0475*
  • Covenant House Greater Washington(ኮቬናንት ሃውስ ግሬተር ዋሺንግተን)
    201 Mississippi Ave SE - (202) 610-9600*+
  • Casa Ruby(ካዛ ሩቢ)
    1635 Connecticut Ave NW - (202) 290-1329*
  • Zoe's Doors(ዞዊስ ዶርስ)
    900 Rhode Island Ave NE - (202) 248-2098*

(*) በእነዚህ አቅራቢዎች ውስጥ ያሉ አገልግሎቶች ሊለያዩ ይችላሉ ነገር ግን ምግብ፣ ልብስ፣ የልብስ ንጽህና አገልግሎቶች፣ ሻወር፣ የጉዳይ አስተዳደር፣ እና ወደ ሌሎች አገልግሎቶች ሪፈራልን ሊያካትቱ ይችላሉ።
(+) ራሱን የቻለ የገንዘብ ድጋፍ።

የድንገተኛ ጊዜ መጠለያዎች

  • Sasha Bruce Youthwork - Bruce House (እድሜያቸው 17 እና ከዚያ በታች ለሆኑ)
    - ለመግባት ይደውሉ ወደ (202) 546-4900
  • Casa Ruby - CR3 (ለLGBTQ ብቻ) (እድሜያቸው ከ18-24 ለሆኑ)
    - 2002 R Street NW - (202) 355-5155
  • Covenant House Greater Washington - The Sanctuary (እድሜያቸው ከ18-24 ለሆኑ)
    - 2001 Mississippi Avenue SE - (202) 610-9698
  • Covenant House Greater Washington - Safe Haven (እድሜያቸው ከ18-24 ለሆኑ)
    - 511 Melon Street SE - (202) 610-9600
  • Healthy Babies – Muriel’s House (እድሜያቸው ከ16-21 የሆኑ ነፍሰጡር ወይም ወጣት ወላጆች)
    - ለመግቢያ ይደውሉ ወደ (202) 396-2809
  • Sasha Bruce Youthwork– Phillip Reid’s Home (18-24 ዓመት)
    - 1814 Rhode Island Ave NE - (202) 948-2869

እርስዎ እድሜዎ ከ 18-እስከ-24 ዓመት ከሆነ (በሽግግር እድሜ ላይ ያለ ወጣት፣ “TAY”) እና ቤት አልባነት ካጋጠሞት፣ Runaway and Homeless Youth (RHY) የስልክ መስመር ጋር ይደውሉ በ (202) 547-7777 ወይም www.coordinatedentry.comበመጎብኘት ‘እርዳታ?’ በሚለው ስር የአውትሪች እና የድሮፕ ኢን ሴንተር(የማህበረሰብ ማዕከላት) ቦታዎችን ዝርዝር ይመልከቱ።

የቤት አልባነት የዳይቨርዥን አገልግሎቶች

ከላይ በተዘረዘሩት የማህበረሰብ አጋሮች ከሚሰጡት አገልግሎቶች በተጨማሪ፣ YSD የወጣቶችን የቤት አልባነት መከላከል፣ የማገናኘት እና የማረጋጋት አገግሎቶችን የሚሰጠውን Youth Housing Options Prevention Education (HOPE) ፕሮግራምን ያስተዳድራል። ፕሮግራሙ ለደህንነት የማያሰጋ እና የሚቻል ሆኖ ሲገኝ የሚዲየሽን (የሽምግልና) አገልግሎቶችን እና የቤተሰብ ድጋፍን በመስጠት፣ እንዲሁም ቋሚ የመኖሪያ ቤት መፍትሄዎችን በመለየት ወጣቶች የቤት አልባ የመጠለያ ስርዓት ውስጥ እንዳይገቡ እና ከተፈጥሯዊ አጋዦቻቸው (ቤተሰብ፣ ሜንቶር፣ አጋሮች፣ ወዘተ) ጋር እንደገና እንዲገናኙ ይሰራል።

ስለ ቤት አልባ ወጣቶች አገልግሎቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ ወደ (202) 698-4334 ይደውሉ።

ቤት ማስለቀቅን የመከላከል እና የቤት ኪራይ እርዳታ

ዲስትሪክቱ ኗሪዎች ከቤት እንዳይለቁ ለመከላከል የሚረዱ የመኖሪያ ቤት የኪራይ እርዳታ እና የመኖሪያ ቤት ግብዓቶች አለው። DHS የመኖሪያ ቤት አለመረጋጋትን እና መፈናቀልን ለመቀነስ፣ እና በCOVID-19/ኮሮናቫይረስ የህዝብ ጤና አደጋ ምክንያት የቤት አልባነት ቁጥር ማሻቀብን ለመከላከል የሚያስችል የተቀናጀ፣ የኤጀንሲዎች የጋራ እቅድ ለማዘጋጀት እና ለመተግበር ከዲስትሪክታችን አጋር ኤጀንሲዎች ጋር በቅርበት እየሰራ ነው።

STAY DC (Stronger Together By Assisting You)

STAY DC የመኖሪያ ቤት እና የአገልግሎት ወጪዎችን ለመሸፈን እና የገቢ ማጣትን ለማካካስ ድጋፍ ለሚፈልጉ የዲሲ አከራዮች እና የመኖሪያ ቤት አቅራቢዎች የፋይናንስ እርዳታ ፕሮግራም ነው። STAY DC ከኦክቶበር 27፣ 2021 ጀምሮ ማመልከቻዎችን አይቀበልም። አሁንም የመኖሪያ ቤት ኪራይ እርዳታ ከፈለጉ፣ ለድንገተኛ ጊዜ የቤት ኪራይ እርዳታ ፕሮግራም (ዝርዝሩን ከታች ይመልከቱ) ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ስለ STAY DC ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሎት፣ እባክዎ [email protected]ያግኙ።

የድንገተኛ ጊዜ የኪራይ እርዳታ ፕሮግራም

የድንገተኛ ጊዜ የኪራይ ድጋፍ ፕሮግራም (ERAP) ከአካባቢው አማካይ ገቢ (AMI) 40% ያነሰ ገቢ ላላቸው እና የመኖሪያ ቤት የድንገተኛ አደጋ ችግር ላጋጠማቸው ብቁ ሆነው ከተገኙ እና የመፈናቀል ስጋት ከተጋረጠባቸው፣ ያልከተከፈለ የቤት ኪራያቸውን የዘገየበት መቀጮ እና የፍርድ ቤት ወጪዎችን ጨምሮ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ያግዛቸዋል። ፕሮግራሙ በተጨማሪ ወደ አዲስ አፓርትመንት ቤት ለሚቀይሩ ሰዎች ተቀማጭ የዋስትና ገንዘብ እና የመጀመሪያ ወር ኪራይ እገዛ ያደርጋል። የብቃት መስፈርቶቹን ለማየት እና ለ ERAP ለማመልከት፣ እባክዎ ይህንይጫኑ።

ስለ ድንገተኛ ጊዜ የመኖሪያ ቤት ኪራይ እርዳታ ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሎት፣ እባክዎ [email protected]ያግኙ።

Homelessness Prevention Program (HPP) (ቤት አልባነትን የመከላከል ፕሮግራም)

Homelessness Prevention Program (HPP) (ቤት አልባነትን የመከላከል ፕሮግራም) ቤት አልባ የመሆን ስጋት ያለባቸው ቤተሰቦች እዚያው ማህበረሰብ ውስጥ ሆነው ቤተሰባቸውን ማረጋጋት የሚችሉበት አገልግሎቶችን እና ግብዓቶችን በመስጠት የመጠለያ ሲስተም ውስጥ እንዳይገቡ ይከላከላል። የዳይቨርዥን አገልግሎቶች በተጨማሪ ከመኖርያ ቤታቸው የተፈናቀሉ ቤተሰቦች ተረጋግተው እንዲኖሩ ወይም ቁሚ መኖሪያ ቤት እስኪመደብላቸው ድረስ ከመጠለያ ውጪ የድንገተኛ ጊዜ መኖሪያ እና ደጋፊ አገልግሎቶችን በመስጠት ለመርዳት ዝግጁ ናቸው።

እርስዎ እድሜያቸው ከ18 በታች ልጆች ያሎት ቤተሰብ ከሆኑ እና የድንገተኛ ጊዜ መጠለያ ካስፈለጎት፣ እባክዎ የመጠለያ የስልክ መስመር ጋር በ (202) 399-7093 ይደውሉ። የመጠለያው የስልክ መስመር 24 ሰዓት በቀን ክፍት ነው።

የወጣት እና የማህበረሰብ አገልግሎቶች

የስደተኛ እርዳታ

DCORR የሚከተሉትን አገልግሎቶች እና/ወይም ጥቅማጥቅሞችን በጊዜ ገደብ ይሰጣል፣

  • የስደተኛ የማህበራዊ አገልግሎቶች (የሥራ ቅጥር እርዳታ፣ የጉዳይ አስተዳደር፣ እና ሌሎች አገልግሎቶች)
  • የስደተኛ የጥሬ ገንዘብ እርዳታ (ብቁ ለሆኑ ስደተኞች ለችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታ (TANF) ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጥሬ ገንዘብ ክፍያን ይሰጣል።)
  • የስደተኛ የጤና ማበረታቻ (የስደተኛ የጤና ሥነ ትምህርት እና የጤና እና የአእምሮ ስሜት አገልግሎቶችን ይደግፋል)
  • የስደተኛ የህክምና እርዳታ( ብቁ ለሆኑ የስደተኛ ማህበረሰብ የህክምና እርዳታን ይሰጣል)
  • የስደተኛ የህክምና ምርመራ (ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገቡ ስደተኞች የህክምና ምርመራ)
  • ብቻቸውን የሆኑ አካለ መጠን ያልደረሱ ስደተኛ ልጆች (URM) ፕሮግራም (ብቻቸውን የሆኑ አካለመጠን ያልደረሱ ስደተኛ ልጆች ወደ አዋቂነት እንዲሸጋገሩ እና ራሳቸውን እንዲችሉ ያግዛል)
  • ወደ አገር የመመለስ አገልግሎቶች(የዩኤስ ዜጎች ከውጭ አገር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ያግዛል)

እነዚህ አገልግሎቶች ለስደተኞች አስፈላጊው ድጋፍ እና እርዳታ መሰጠቱን ለማረጋገጥ ከአገልግሎት አቅራቢዎች ኔትወርክ ጋር በመተባበር የሚሰጡ ናቸው።

የአገልግሎት አድራሻ፣ Refugee Resettlement Office, (202) 698-4316

የቤት ውስጥ ጥቃት ሰለባዎች ድጋፎች

ለማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት አቅራቢዎች በሚደረገው እርዳታ አማካኝነት፣ DHS የቤት ውስጥ ጥቃትን የሚከላከሉ እና ከእንደዚህ ዓይነት ክስተቶች የሚያገግሙ ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን የሚረዱ ፕሮግራሞችን እና ፕሮጀክቶችን ማቋቋም፣ ማቆየት፣ እና ማስፋፋትን ይደግፋል።

አገልግሎቶች

  • የድንገተኛ ጊዜ እና የሽግግር ጊዜ መጠለያ
  • የጉዳይ አስተዳደር
  • ምክር(ካውንስሊንግ)/ሙግት
  • አውትሪች/ትምህርት

የ DHS DV አቅራቢዎች ዝርዝር ለማግኘት፣ ይህን ይጫኑ።

የወጣት አገልግሎቶች ክፍል (YSD)

YSD ቤተሰቦችን የሚያጠናክር፣ ከመኖሪያ ቤት አለመረጋጋት ጋር የተያያዙ ስጋቶችን የሚቀንስ፣ የትምህርት ቤት ክትትልን የሚያሻሽል፣ በችግር ውስጥ ያሉ ወጣቶችን የሚያረጋጋ፣ እና የፍርድ ቤት ተሳትፎን የሚቀንስ ነጻ አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን ለወጣቶች ይሰጣል። YSD በርካታ ዋና ፕሮግራሞችን ያካትታል እና ፈታኝ ባህርዮችን እና ሁኔታዎችን ለመቅረፍ ወጣቶችን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ማህበረሰብን መሰረት ያደረጉ አቅራቢዎችን እና የዲስትሪክት ኤጀንሲዎችን ያሳትፋል።

የወጣት አገልግሎቶች ክፍል አምስት የተለዩ ፕሮግራሞችን ያካትታል፣

  • Alternatives to the Court Experience (ACE) Diversion Program*፣ ይህ የዳይቨርዥን ፕሮግራም ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ቢሮ (OAG)፣ ከሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት (MPD)፣ እና ከፍርድ ቤት የማህበረሰብ አገልግሎቶች (CSS) ጋር በመተባበር የሚሰራ እና ከዲስትሪክቱ የወጣት ጥፋተኞች የፍትህ ተቋማት ለሚመጡ ሁሉም ዳይቨርዥኖች እንደ አንድ መግቢያ በር ሆኖ ያገለግላል። አግባብ የሆኑ ሁኔታዎች ሲኖሩ፣ መንግስት የስታተስ ወንጀሎችን በመፈጸም የተጠረጠረን ወጣት ላይ ክስ አለመመስረትን ይመርጣል (ለምሳሌ መቅረት እና ማምለጥ) እና/ወይም ቀላል የወንጀል ድርጊቶች። የ ACE ዋነኛ ዓላማ እድሜያቸው እስከ 18ዓመት ድረስ የሆናቸውን ወጣቶችን ከመክሰስ ይልቅ አገልግሎቶችን እና የማህበረሰብ ድጋፎችን በመስጠት በፍርድ ቤት ሂደት የሚያልፉትን ቁጥራቸውን መቀነስ ነው። ማስታወሻ፥ ሪፈራሎች ወደ ACE የሚመጡት በ MPD ወይም OAG አማካኝነት ብቻ ነው። ስለ ACE ፕሮግራም ጥያቄዎች ካሎት፣ እባክዎ ኢሜይል ይላኩ ወደ፣
    [email protected]
     
  • Parent and Adolescent Support Services Intensive Case Management (PASS ICM) ከትምህርት ቤት የሚፎርፉ (የሚቀሩ)፣ ያለፈቃድ ከቤት የሚወጡ፣ ወደ ቤት ከሰዓት እላፊ በኋላ የሚመለሱ፣ እና/ወይም ቤት ውስጥ እና/ወይም ከቤት ውጭ ከፍተኛ የሆነ ያለመታዘዝን የሚያሳዩ እድሜያቸው ከ10 እስከ 17 ዓመት የሆናቸው ወጣቶችን ይረዳል። PASS ICM ወጣቶች የወጣት ጥፋተኞች የፍትህ ስርዓት እና/ወይም የልጅ ዌልፌር ሲስተም ውስጥ እንዳይገቡ የማድረግ ዋነኛ ግቡን ለማሳካት፣ ለሚያገለግላቸው ወጣቶች እና ቤተሰቦች የቀደመ የጣልቃገብነት አገልግሎቶችን ይሰጣል። PASS ICM ራስን ወደ መቻል የሽግግር ሂደቱን ከባህርይ ጤና ዲፓርትመንት ጋር በአጋርነት ይጠቀማል፣ ይህም የስሜታዊ እና የባህርይ ችግሮች ያሉባቸው በእድሜ ተለቅ ያሉ ወጣቶች የጉዳይ አስተዳደር ነው። የPASS ICM አገልግሎቶችን የሚያገኙ ሁሉም ወጣቶች እንደ ሜንቶሪንግ፣ ቱቶሪንግ(ማስጠናት)፣ እና ከትምህርት ሰዓት በኋላ የትምህርት ቤት ፕሮግራሞችን የመሳሰሉ የማህበረሰብ ድጋፎችን ያገኛሉ። ሪፈራሎች በ PASS ሪፈራል ቅጽ ወይም በኢሜይል፣ ፋክስ፣ ስልክ ወይም አማካኝነት ሊደረጉ ይችላሉ። የኢሜይል አድራሻ፣ [email protected]
     
  • Strengthening Teens Enriching Parents (STEP) Program* መጥፋታቸው ለ MPD ሪፖርት የተደረገ እድሜያቸው እስከ 17ዓመት ከሆናቸው ወጣቶች ጋር ይሰራል። የጉዳይ አስተዳዳሪዎች ወጣቱ ለምን ከቤት እንደወጣ ለመገምገም እና፣ ከቤተሰቡ ጋር በመሆን ከማህበረሰብ አጋሮች እና ከሌሎች የዲስትሪክት ኤጀንሲዎች ጋር አገልገሎቶቹን በመተግበር ወደፊት MPRs(የጠፉ ሰዎች ሪፖርት) የመከሰት እድሉን ለመቀነስ እና የቤተሰብ መረጋጋትን ይጨምራሉ። ወደ STEP ፕሮግራም ሪፈራል ሊመጣ የሚችለው በ MPD አማካኝነት ብቻ ነው።
     
  • ስለ STEP ፕሮግራም ጥያቄዎች ካሎት፣ እባክዎ ኢሜይል ይላኩ ወደ [email protected]
     
  • Teen Parent Assessment Program (TPAP) ነፍሰጡር ወይም ወጣት ወላጆች ራሳቸውን ወደ መቻል እንዲሸጋገሩ እና ተጨማሪ ያልተፈለገ እርግዝና እንዲቀንስ ለማስቻል ይሰራል። TPAP የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዲፕሎማ ወይም አጠቃላይ ተመጣጣኝ ዲፕሎማ (GED) ለሌላቸው ወጣቶች የትምህርት ብቃት ደረጃቸውን በመጨመር ራስ መቻልን ለማበረታታት ከሰብዓዊ አገልግሎቶች የኢኮኖሚ ዋስትና አስተዳደር (ESA) ጋር በአጋርነት ይሰራል። ነፍሰጡር ወይም ወጣት ወላጆች፣ የ TPAP ንቁ ተሳታፊዎች እንደመሆናቸው ወጣቶች ወደ አዋቂነት በተሳካ ሁኔታ እንዲሸጋገሩ እንደሚረዳ በማስረጃ ላይ በተመሰረተው የጣልቃገብነት ሞዴል በሆነው ከሽግግር ጊዜ ወደ ራስን መቻል ሂደት (TIP) ሞዴል በመጠቀም የጉዳይ አስተዳደር አገልግሎቶችን ያገኛሉ። ማንኛውም ሰው ይህን የሪፈራል ቅጽ በመሙላት ወይም ኢሜያል በመላክ ወይም ወደ 202-698-4334 በመደወል ለTPAP ሪፈራል ማስገባት ይችላል።

YSD በተጨማሪ ሁለት የስፔሺያሊቲ አገልግሎቶችን ያካትታል፣

  • Functional Family Therapy (FFT)  ሪፈር የተደረጉትን የተለዩ ባህርዮች (ለምሳሌ፣ የሰዓት እላፊ ጥሰቶችን፣ ማምለጥ፣ እና መቅረት) ለመቅረፍ የቤት ውስጥ የቤተሰብ ካውንስሊንግ የሚሰጥ እና ወጣት ጥፋተኝነትን ደግሞ ግንኙነት እና ቤተሰብ ላይ በማተኮር የቤተሰብ ግንኙነቶችን የሚያሻሽል፤ጥልቅ፣ የአጭር ጊዜ የቴራፒዩቲክ ሞዴል ነው። ብቃት፣ FFT እድሜያቸው ከ10 እስከ 17 ዓመት ልጆች ላላቸው የዲሲ ኗሪዎች የበጎ ፈቃደኛ ፕሮግራም ነው። ማንኛውም ሰው ወደ FFT ሪፈር ማድረግ ይችላል። ሪፈራል በኢሜይል፣ በፋክስ ወይም በስልክ ሊደረግ ይችላል። የኢሜይል አድራሻ፣ [email protected]
    የስልክ አድራሻ፣ (202) 698-4334
     
  • PASS Crisis and Stabilization Team (PCAST) ከማህበረሰቡ ሪፈራሎችን ይቀበላል እና እድሜያቸው ከ11-17 ለሆኑ ልጆች እንዲሁም ችግር ላይ ላሉ ልጆቻቸው የችግር ምዘና፣ የጣልቃገብነት፣ እና የማረጋጊያ አገልግሎቶችን ይሰጣል። የሚሰጡት አገልግሎቶች የማህበረሰብ ግብዓቶችን በመጠቀም የቤተሰብ ጥበቃ/እንደገና ማገናኘትን ለማመቻቸት የአውትሪች፣ የተሟጋች፣ እና የአገልግሎት ቅንጅትን ያካትታሉ። በተጨማሪ፣ PCAST የመላመድ ችሎታዎችን ለማሻሻል እና ወይም ለመጨመር የሚሰራ ሲሆን ይህም ወጣቶች እና ቤተሰቦች የመረጋጋት ብቃት እንዲኖራቸው ያስችላል። ሪፈራሎች በኢሜይል፣ ፋክስ፣ ስልክ ወይም በ PASS ሪፈራል ቅጽ አማካኝነት ሊደረጉ ይችላሉ። የኢሜይል አድራሻ፣ [email protected]። የስልክ አድራሻ፣ (202) 698-4334

የቤተሰብ የቀውስ(ችግር) ድጋፍ

The Strong Families Program ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት ኗሪዎች የመከላከል/ቀዳሚ የጣልቃገብነት ፕሮግራም ነው። Strong Families የግለሰብ ወይም የቤተሰብ መበታተንን ወይም መለያየትን ሊያስከትል የሚችል ችግር ውስጥ ያሉ እና፣ በርካታ ውስብስብ ተግዳሮቶች ያሉባቸውን በመላው ከተማ ውስጥ ያሉ ተጋላጭ ግለሰቦችን እና ቤተሰቦችን ለመርዳት የሚያስችል መዋቅር ነው።

The Strong Families Program የሚከተሉት ነገሮች ሲያጋጥምዎ እርስዎን እና ቤተሰብዎን ሊረዳ የሚችል ነው፤ የእሳት አድጋ፣ የህንጻ መዘጋት፣ ትችት፣ ወይም ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ።

The Strong Families Program የተለያዩ ማዕቀፍ ያላቸው የማህበራዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል። እነዚህም የደምበኞችን ፍላጎት መገምገም፣ የጉዳይ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፣ የአጭር ጊዜ የማህበራዊ ስራ ጣልቃገብነት እና ከዲስትሪክት እና ከማህበረሰብ ኤጀንሲዎች ጋር ሪፈራል እና አገልግሎቶችን ማስተባበር ያካትታሉ።

ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎ አጠቃላይ የመረጃ ቁጥር ጋር በ (202) 698-4293 ይደውሉ።

Gen2Gen DC

Gen2Gen DC ፕሮግራሞች እርስዎ እና መላው ቤተሰቦችዎ ሙሉ አቅማችሁ ላይ እንድትደርሱ ለማገዝ የሚያስችል የድጋፍ አገልግሎቶችን ለመስጠት የታቀደ ነው። እያንዳንዱ ፕሮግራም የወላጆችን፣ የልጆች እና የአያቶችን ፍላጎቶችን ለማካተት፣ የብዙ ትውልድ አቀራረብን ያካትታል። በማህበረሰብዎ ውስጥ ካሉ ግብዓቶች እና ድጋፎች ጋር እርስዎን በሚያገናኙ ፕሮግራሞች አማካኝነት የግል፣ የሥራ ቅጥር፣ የትምህርት እና የመኖሪያ ቤት ግቦችዎን ለማሳካት እርዳታ ማግኘት።

ለበለጠ መረጃ፣ እባክዎ ይደውሉ ወደ (202) 698-4722 ወይም ኢሜይል ያድርጉ ወደ [email protected].

ስጋትን እንዴት ማስገባት ይቻላል

የፕሮግራም ግምገማ፣ ቁጥጥር፣ እና ምርመራ ቢሮ (OPRMI) ቀድሞ Food Stamps Program (ፉድ ስታምፕስ ፕሮግራም)(FSP) ተብሎ ይታወቅ የነበረውን የተጨማሪ ምግብ እርዳታ ፕሮግራም(SNAP)፣ የችግረኛ ቤተሰቦች ጊዜያዊ እርዳታ (TANF) እና Medicaid የህዝብ እርዳታ ጥቅማጥቅም የማጭበርበር ወንጀል ጥርጣሬዎችን ይመረምራል። በማስረጃ የተደገፉ ጉዳዮች ወደ ክስ ሊመሩ ወይም ከፕሮግራም መሰረዝን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

OPRMI በተጨማሪ የመጠለያ ቁጥጥር ለማድረግ እና በተሻሻለው የ2005 የቤት አልባ አገልግሎቶች ማሻሻያ ህግ (HSRA) የተሸፈኑ ቀጣይነት ያላቸው የኮሎምቢያ ዲስትሪክት ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን የመገምገም ሀላፊነት አለው። እነዚህ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች አቤቱታዎችን፣ ቅሬታዎችን፣ እና ስጋቶችን መፍታትን ያካትታሉ።

OPRMI በተጨማሪ ያልተለመዱ ክስተቶችን ይመረምራል፤ ለምሳሌ የኮንትራክተር ብልሹ ባህርይ፣ የሠራተኛ ብልሹ ባህርይ፣ ትንኮሳ፣ እና ጥቃት፣ ወይም የDHS ፕሮግራሞችን ታማኝነት ሊጎዳ የሚችል ወይም የDHS ደምበኞችን፣ የዲስትሪክቱ የመንግስት ሠራተኞችን እና የህዝቡን ጤና ወይም ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውም ጉዳይ።

በተጨማሪ፣ OPRMI የማሻሻያ ሀሳቦችን ይቀበላል እንዲሁም ይመረምራል እና ከ DHS ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ የቀረቡ አቤቱታዎችን ለመፍታት ያስተባብራል።

ማንኛውም ሰው አቤቱታ፣ አስተያየት፣ ያልተለመደ ክስተት፣ ወይም የማጭበርበር ጥርጣሬን ወደ [email protected] ኢሜይል በማድረግ ማቅረብ ይችላል።

የአድራሻ መረጃ፥

64 New York Avenue, NE, 6th floor
Washington, DC 20002
ስልክ ቁጥር፥ (202) 671-4200
ፋክስ፣ (202) 671-4326  • TTY: 711
ኢሜይል፣ [email protected]