Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dhs

DHS


 

Director Laura Green Zeilinger Honored with Outstanding Local Leader Award. Read more

 

Office of Migrant Services Mission Anniversary Abstract. Learn more
 

coronavirus.dc.gov

 

 

Pandemic Electronic Benefits Transfer (P-EBT) Program (አማርኛ)

የP-EBT ካርድ እትሞች ቅጽ፡- English – (Español) Spanish – (አማርኛ) Amharic.

ከሴፕቴምበር 30፣ 2021 ጀምሮ ከ6 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ለ2021-2022 እና ለበጋ 2022 ክፍያዎች ተሰጥተዋል። የክፍያው መጠን አንድ ልጅ ብቁ በሆነበት ወራት ብዛት ይለያያል። በሴፕቴምበር 30፣ 2021 ከ6 አመት በታች የሆኑ እና በትምህርት አመቱ SNAP የተቀበሉ ቤተሰብ አባል የሆኑ ልጆች ብቻ ለዚህ ክፍያ ብቁ ናቸው። የበጋ 2022 ጥቅማጥቅሞች ለሁሉም ብቁ ለሆኑ ልጆች በሴፕቴምበር 2022 መጨረሻ ላይ እንዲሰጡ ታቅዶላቸዋል።

የP-EBT ፕሮግራም መረጃ እና ወቅታዊ ነገሮች

የወረርሽኝ ጊዜ የኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅሞች ማስተላለፊያ (ፓንዴሚክ ኤሌክትሮኒክ ቤኔፊትስ ትራንስፌር) (P-EBT) ፕሮግራም በኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅሞች ማስተላለፊያ (EBT) ካርድ ላይ የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ይሰጣል። ጥቅማጥቅሞቹ በህዝብ ጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የበአካል ትምህርትን የሚገደቡ ገደቦች ባይኖሩ፣ በትምህርት ቤት ወይም የልጅ እንክብካቤ ውስጥ በመደበኛነት ነጻ ወይም የቅናሽ-ዋጋ ምግቦችን ይቀበሉ የነበሩ ብቁ ልጆች ላላቸው የዲስትሪክት ቤተሰቦች ይሰጣሉ።  ቤተሰቦች P-EBT ለመቀበል ማመልከት አይችሉም። ጥቅማጥቅሞች የብቁነት መስፈርቶችን ለሚያሟሉ ወዲያውኑ ይከፈላሉ።

የP-EBT ጥቅማጥቅሞች ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም (ሰፕሊሜንታል የኒዩትሪሽን አሲስታንስ ፕሮግራም) (SNAP -- ከዚህ በፊት ፉድ ስታምፕ ተብሎ ይታወቃል) ከሚቀበሉ መደብሮች ወይም ኦንላይን ከ Amazon ወይም Aldi ምግብ ለመግዛት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላል። ቤተሰቦች የማስተላለፊያ ታሪካቸውን ለማየት፣ ቀሪ ህሳባቸውን ለማየት፣ ወይም የ EBT ካርድን የሚቀበሉ የችርቻሮ ነጋዴዎችን ለማግኘት ebtEDGE.com መጎብኘት ወይም የebtEDGE የሞባይል መተግበሪያን ከአፕል ወይም የጉግል ጨዋት ክምችት ላይ ማውረድ ይችላሉ።

የP-EBT ጥቅማጥቅሞች ለበጋ 2022

በጁላይ 2022፣ የ USDA የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት (ፉድ ኤንድ ኒዩትሪሽን ሰርቪስ) (FNS) የበጋ 2022 ጥቅማጥቅሞችን ለኮሎምቢያ ዲስትሪክት አጽድቋል። ዲስትሪክቱ ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች በሴፕቴምበር 2022 መጨረሻ ላይ ጥቅማጥቅሞችን ያወጣል። ብቁ የሆኑ ህጻናት ለበጋው በፌዴራል የጸደቀ ቁርጥ መጠን $391 በአንድ ልጅ ይቀበላሉ።

የP-EBT ብቁነት ለበጋ 2022

የDC ህጻናት በሚከተሉት ሁኔታዎች ስር ለበጋ 2022 የP-EBT ጥቅማጥቅሞች ብቁ ይሆናሉ፥

  1. ለበጋ P-EBT ብቁ ለመሆን፣ ከስድስት ዓመት በላይ እድሜ ያለው/ላት ልጅ፣ ለ SY2021- 2022፣ ከሚከተሉት አንዱን ያደረገ/ች መሆን አለበት/ባት፥
    • የህብረተሰብ ብቁነት ድንጋጌዎች (ኮሙኒቲ ኤሊጂብሊቲ ፕሮቪዥንስ) (CEP) ትምህርት ቤት ውስጥ መመዝገብ ወይም
    • ብሔራዊ የትምህርት ቤት ምሳ ፕሮግራም (ናሽናል ስኩል ላንች ፕሮግራም) (ማስፈንጠሪያ ይጨምሩ) ውስጥ የሚሳተፍ ትምህርት ቤት ውስጥ መመዝገብ
      • እና ለ ነጻ እና ቅናሽ-ዋጋ ምግቦች (ፍሪ ኤንድ ሪዲዩስድ-ፕራይስ ሚልስ) (FARM) ከኦገስት29, 2022 በፊት ያመለከቱ (እና የጸደቀላቸው) ወይም
      • በትምህርት ቤታቸው ለ FARM በምድብ የጸደቀላቸው (SNAP እና TANF የሚቀበሉ ተማሪዎችን የሚያካትት)
         
  2. ከ6 ዓመት በላይ የሆነ/ች ልጅ በጁን ውስጥ ብቁ ካልሆነ/ች፣ ነገር ግን ቤተሰቦቻቸው የገቢ ለውጥ ካጋጠማቸው፣ ቤተሰቦቻቸው ለ ነጻ እና ቅናሽ-ዋጋ ምግቦች(FARM) ለበጋ-2022 ከኦገስት 29 ማመልከት ይችላሉ። የልጃቸው ትምህርት ቤት ማመልከቻውን ካጸደቀ፣ ከኦክቶበር በፊት የበጋ P-EBT ይቀበላሉ።
     
  3. ለበጋ P-EBT ብቁ ለመሆን፣ በሴፕቴምበር 30, 2021 ከ6 ዓመት በታች የሆነ/ች ልጅ ከኦገስት 30፣ 2021 እና ኦገስት 20, 2022 መካከል የSNAP ጥቅማጥቅም የሚቀበል ቤተሰብ አካል መሆን ይኖርበታል/ታል።

የP-EBT ጥቅማጥቅሞች ከ6 ዓመት በታች (SY 2021-2022) ለሆኑ ህጻናት

ዲስትሪክቱ በጁላይ 2022 ላይ P-EBTን ለ ትምህርት ዓመት 2021-2022 የልጅ እንክብካቤን ተግባራዊ ለማድረግ የመጽደቅ ደብዳቤ ደርሶታል።  በሴፕቴምበር 30, 2021 እድሜያቸው ከ6 ዓመት በታች የነበሩ እና የ SNAP ተሳታፊ ቤተሰብ አካል የሆኑ ህጻናት በ SNAP ውስጥ የተመዘገቡበት ወር ወርሃዊ የ$60.20 በወር ጥቅማጥቅም ወይም ለዓመቱ $602.02 ያገኛሉ። እንዲሁም እነዚህ ህጻናት ለበጋው ቁርጥ $391 ጥቅማጥቅም ያገኛሉ።

የP-EBT ካርድ መስጠት

ባሁን ጊዜ የSNAP ጥቅማጥቅሞችን እየወሰዱ ያሉ ወይም ከዚህ በፊት የP-EBT ጥቅማጥቅሞችን የወሰዱ ብቁ የሆኑ ቤተሰቦች በነባሩ የ EBT ካርዳቸው ላይ ጥቅማጥቅሞች ይገቡላቸዋል። ለ P-EBT ፕሮግራም አዲስ የሆኑ ቤተሰቦች ለልጃቸው ወይም ልጆቻቸው ጥቅማጥቅሞች ሲወጡ አዲስ የ EBT ካርዶችን ይቀበላሉ። ስለዚህ፣ ቤተሰቦች በትምህርት ቤታቸው ወይም በDHS ለSNAP ጉዳያቸው ወቅታዊ የሆነ አድራሻ በፋይል ላይ መኖራቸው አስፈላጊ ነው።

የP-EBT ጥሪ ማእከል እርዳታ፣ በካርድ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ

ቤተሰቦች የጠፋ ወይም የተበላሸ የEBT ካርድን ሪፖርት ማድረግ፣ ወይም የEBT ካርድን እንዲሰራ ማስጀመር ጋር ለተያያዙ ችግሮች እርዳታ ማግኘት ይችላሉ፣ ለFISን፣የዲስትሪክቱ የEBT አጋር የሆነውን፣ በቀን 24 ሰዓታት፣ በሳምንት 7 ቀናት በነጻ የስልክ መስመራቸው (888) 304-9167 በመደወል። FIS አድራሻን ማሻሻል አይችልም። አድራሻዎ ከተቀየረ እና የመተኪያ ካርድ ካስፈለገዎ፣ መተኪያውን ከመጠየቅዎ በፊት ትክክለኛ አድራሻ በDHS ፋይል ላይ መኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብዎታል።

አጠቃላይ መረጃ ስለ  EBT ካርዶች

ስለ P-EBT እና የEBT ካርድ ማስጀመሪያ፣ አጠቃቀም፣ አስተዳደር፣ እና ቀሪ ህሳቦችን በተመለከተ አጠቃላይ መረጃ፣ በ https://dhs.dc.gov/page/ebt-card-updates ይገኛል።

ተጨማሪ የዲስትሪክት የምግብ መጠቀሚያዎች እና የህዝብ ጥቅማጥቅሞች

በኮሮናቫይረስ/COVID-19 የህዝብ ጤና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት በዲስትሪክቱ ውስጥ ያሉ የምግብ መጠቀሚያዎች በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በ coronavirus.dc.gov/food ወይም የ DHS የምግብ መጠቀሚያዎች መረጃ ገጽ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም (SNAP) ውስጥ ለመሳተፍ ብቁ ሊሆኑ የምችሉ ቤተሰቦች እንዴት እንደሚያመለክቱ የሚገልጽ መረጃን በ https://dhs.dc.gov/service/apply-benefits"https://dhs.dc.gov/service/apply-benefits ማግኘት ይችላሉ።

ተጨማሪ መረጃ

እንዲሁም ተጨማሪ የፕሮግራም መረጃን ለማግኘት፣ ቤተሰቦች ለESA የህዝብ ጥቅማጥቅሞች ማእከል በ 202-727-5355 መደወል ይችላሉ። የግለሰባዊ ጉዳይ ችግሮች ላይ መርዳት አይችሉም። ጥቅማጥቅሞችዎ ትክክል እንዳልነበረ ካሰቡ ወይም በፋይል ላይ አድራሻዎን መቀየር ካስፈለገዎ፣ የጉዳይዎን መረጃ የያዘ የድረገጽ ቅጽን ማስገባይ ይኖርብዎታል፣ እዚህ፥ English – (Español) Spanish – (አማርኛ) Amharic.