Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

dhs

DHS


 

Notice of revisions to the Emergency Rental Assistance Program (ERAP) Portal RE-OPENING schedule for fiscal year 2025. Read more

 

Want to help? Here is how. Learn more

 

There is a Temporary Local Benefit to households receiving the Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP) for the period January 1, 2024, through September 30, 2024. Learn more

 

List Your Units Here Today! Read more

 

የወረርሺኝ የኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅሞች ዝውውር (P-EBT) ፕሮግራም

የP-EBT ካርድ እትሞች ቅጽ፡- English – (Español) Spanish – (አማርኛ) Amharic.

በኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅሞች ዝውውር (P-EBT) ፕሮግራም ላይ ስላለዎት ፍላጎት እናመሰግናለን። የP-EBT ፕሮግራም አሁን ያበቃ ሲሆን DHS በP-EBT ካርዶች ላይ ምንም አይነት ተጨማሪ ለውጦችን ማድረግ አይችልም። ምትክ የP-EBT ካርድ ከፈለጉ፣ እባክዎን ለFIS ይደውሉ ወይም ከዚህ በታች በ P-EBT ካርድን ማግበር ወይም መተካት የሚለው ክፍል ላይ ከተዘረዘሩት የEBT ካርድ ማከፋፈያ ማዕከላችን አንዱን ይጎብኙ።

P-EBT ትምህርት ቤቶች በCOVID-19 የህዝብ ጤና ድንገተኛ ጊዜ (PHE) ምክንያት ተዘግተው ወይም በተቀነሰ የጊዜ ሰሌዳ ሲሰሩ በነበረበት ጊዜ ብቁ የሆኑ ልጆች ያለፋቸውን የትምህርት ቤት ምግቦች ለማሟላት በፌደራል ህግ በማርች 2020 ተዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን በልጅ እንክብካቤ ውስጥ ያሉ ብቁ ህጻናትን ለማካተት በኦክቶበር 2020 ተስፋፋ። የP-EBT የጥቅማጥቅም መጠኖች እና የብቁነት መስፈርቶች ከታች ባለው ቻርት ላይ በተዘረዘረው መሰረት የፌደራል ህግ ላይ በተደረጉ ለውጦች ምክንያት በጊዜ ሂደት ተለውጠዋል። 

የኮሎምቢያ ዲስትሪክት (“ዲስትሪክት” ወይም “ዲሲ”) ዲፖርትመንት ኦፍ ሂዩማን ሰርቪስስ፣ ከዲሲ ኦፊስ ኦፍ ዚ ስቴት ሱፐርኢንተንደንት ኦፍ ኤጁኬሽን ጋር በአንድነት ፕሮግራሙን በየአመቱ በትምህርት ዘመን (SY) 2019-2020 እና 2022-2023 መካከል አስተድዳሯል። ስለ ሽፋን እና የጥቅማጥቅም መጠኖች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች የ P-EBT ብቁነት እና ክፍያዎችን ይመልከቱ። 

የP-EBT ፕሮግራም በካፒታል ተደራሽነት የኤሌክትሮኒክ ጥቅማጥቅም ሽግግር (Capital Access Electronic Benefits Transfer, EBT) ካርድ የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ይሰጣል። የP-EBT ጥቅማጥቅሞች ተጨማሪ የምግብ እርዳታ ፕሮግራም (SNAP) ጥቅማጥቅሞችን በሚቀበሉ መደብሮች ወይም በመስመር ላይ አማዞን (Amazon) እና አልዲ (Aldi)ን ጨምሮ በተሳታፊ ነጋዴዎች ላይ ምግብ ለመግዛት ሊያገለግሉ ይችላሉ።  

የP-EBT ብቁነት እና ክፍያዎች 

ዲስትሪክቱ በSY 2019-2020 እና 2022-2023 መካከል በየአመቱ ብቁ ለሆኑ የትምህርት ቤት ተማሪዎች የP-EBT ጥቅማጥቅሞችን ሰጥቷል። ለP-EBT ብቁ ለመሆን፣ አንድ ልጅ በብሄራዊ ትምህርት ቤት የምሳ ፕሮግራም (NSLP) ውስጥ በሚሳተፍ ትምህርት ቤት ነጻ እና የቅናሽ ዋጋ ምግቦችን (FARM) ለማግኘት ፈቃድ ማግኘት አለበት። በትምህርት አመቱ የትምህርት ቤቶችን ዝርዝር እና የብቁነት መስፈርቶች ለማግኘት የትምህርት ቤቱን ዝርዝር ይመልከቱ። ለእያንዳንዱ የትምህርት አመት የሽፋን እና የጥቅማጥቅሞች መጠኖች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። 

የትምህርት ቤት ተማሪዎች የP-EBT ጥቅማጥቅሞች 

የትምህርት አመት

የብቁ የሆኑ ተማሪዎች

የጥቅማጥቅሞች መጠኖች

SY 2022-2023

በSY 2022-2023 መጨረሻ በNSLP ትምህርት ቤት ለFARM ፈቃድ አግኝቷል

ለበጋ 2023 $120.00

SY 2021-2022

በSY 2021-2022 መጨረሻ በNSLP ትምህርት ቤት ለFARM ፈቃድ አግኝቷል

ለበጋ 2022 $391.00

SY 2020-2021

በትምህርት አመት ጊዜው ለክፍያ ሽፋን ወር እና ለበጋ ክፍያ በSY 2020-2021 መጨረሻ በNSLP ትምህርት ቤት ለFARM ፈቃድ አግኝቷል

በትምህርት አመቱ (ከኦክቶበር 2020 እስከ ጁን 2021) በወር $122.76 (ትምህርት ቤቱ ለዚያ ወር ሙሉ በሙሉ ሩቅ ካልሆነ ይቀነሳል)፣ እንዲሁም ለበጋ 2021 $375.00

SY 2019-2020

በNSLP ትምህርት ቤት ለFARM ፈቃድ አግኝቷል

ከማርች 2019 እስከ የትምህርት አመቱ መጨረሻ $387.60፣ ተማሪው ከማርች 2019 በኋላ ፈቃድ ካገኘ በጥቅማጥቅሞች ተሰራጭቷል።

የ P-EBT ጥትቅማጥቅሞች ለህጻን እንክብካቤ ተሳታፊዎች 

ከኦክቶበር 2020 ጀምሮ፣ የዩናይትድ ስቴትስ የግብርና ዲፓርትመንት (ዩ.ኤስ.ዲ.ኤ.) DHS በእያንዳንዱ የትምህርት አመት ከኦክቶበር 1 ጀምሮ እድሜያቸው ከስድስት (6) አመት በታች ለሆኑ ህጻናት እና ለክፍያ ሽፋን ወር የSNAP ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኝ ቤተሰብ አካል ለነበሩ የP-EBT ጥቅማጥቅሞችን እንዲያቀርብ ፈቃድ ሰጥቷል። ለእያንዳንዱ የትምህርት አመት የሽፋን እና የጥቅማጥቅሞች መጠኖች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። 

የትምህርት አመት

ብቁ ህጻናት

የጥቅማጥቅሞች መጠኖች

SY 2022-2023

በኦክቶበር 1፣ 2022 ከስድስት አመት በታች (6) እና ለክፍያው ሽፋን ወሩ የSNAP ጥቅማጥቅሞችን የሚቀበል የቤተሰብ አካል

PHE በስራ ላይ በነበረበት የትምህርት ዘመን በወር $50.36 (ከኦገስት 2022 እስከ ሜይ 11፣ 2023)

SY 2021-2022

በኦክቶበር 1፣ 2021 ከስድስት አመት በታች (6) እና ለክፍያው ሽፋን ወሩ የSNAP ጥቅማጥቅሞችን የሚቀበል የቤተሰብ አካል

በትምህርት አመቱ (ከኦገስት 2021 እስከ ሜይ 2022) በወር $60.20፣ እንዲሁም ለበጋ 2022 $391.00

SY 2020-2021

በኦክቶበር 1፣ 2020 ከስድስት አመት በታች (6) እና ለክፍያው ሽፋን ወሩ የSNAP ጥቅማጥቅሞችን የሚቀበል የቤተሰብ አካል

በትምህርት አመቱ (ከኦክቶበር 2020 እስከ 2021) በወር $122.76፣ እንዲሁም ለበጋ 2021 $375.00

የ P-EBT ካርድ መረጃ እና እገዛ 

በአሁኑ ጊዜ የSNAP ጥቅማጥቅሞችን እየተቀበሉ ያሉ ወይም ከዚህ ቀደም የP-EBT ካርድ የተቀበሉ ብቁ የሆኑ ቤተሰቦች በነባር የEBT ካርዳቸው ጥቅማጥቅሞች የሚያገኙ ይሆናል። ለPEBT ፕሮግራም አዲስ የሆኑ ተማሪዎች፣ እንዲሁም ቀደም ሲል በቤተሰባቸው ነባር የSNAP EBT ካርድ P-EBT የተቀበሉ ነገር ግን ከእንግዲህ እነዚያን ጥቅማጥቅሞችን ማግኘት የማይችሉ ተማሪዎች፣ ለልጁ ጥቅማጥቅሞች ሲሰጡ አዲስ የEBT ካርድ ተልኮላቸው ነበር። ሁሉም አዳዲስ የP-EBT ካርዶች የሚሰጡት በልጁ ስም ሲሆን፣ የቆዩ ካርዶች በልጁ ወይም በወላጅ/አሳዳጊ ስም በመዝገብ ላይ ሊሆኑ ይችላሉ። 

እንዲሁም ebtEDGE.comን መጎብኘት ወይም የግብይት ታሪክን እና ቀሪ ሂሳቦችን ለማየት ወይም የP-EBT ካርዱን የሚቀበሉ ቸርቻሪዎችን ለማግኘት የebtEDGE የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያን ከአፕል ወይም ጎግል ፕሌይ መደብር ማውረድ ይችላሉ። 

የP-EBT ካርድን ማግበር ወይም መተካት 

ምትክ የP-EBT ካርድ ከፈለጉ፣ እባክዎን ለFIS፣ የዲስትሪክቱ የEBT ሻጭ በ(888) 304-9167 ይደውሉ። እባክዎን FIS በመዝገቡ ላይ ያለውን አድራሻ ማዘመን እንደማይችል ያስታውሱ። በፋይል ላይ ያለፈበት አድራሻ በሚኖርበት ጊዜ፣ ከሚከተሉት የEBT ካርድ ማከፋፈያ ማዕከላት በአንዱ የP-EBT ካርድ መውሰድ ይችላሉ። 

የስራ ሰአታት ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ7:30 am እስከ 4:45pm ናቸው። እባክዎን ሰአታት እና ቀናት ሊለውጡ እንደሚችሉ ያስታውሱ። የEBT ካርድዎን ማግበርን በሚመለከት መመሪያዎች ወይም የEBT ካርድ ማከፋፈያ ማእከላትን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ማግኘት ይችላሉ።  

ተጨማሪ የዲስትሪክት የምግብ መጠቀሚያዎች እና የህዝብ ጥቅማጥቅሞች 

በዲስትሪክቱ ውስጥ የሚገኙትን የምግብ መርጃዎች በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በዚህ መመሪያ ላይ እንዲሁም እዚህ ይገኛል።  

በSNAP ወይም በDHS በሚቀርቡ ሌሎች የጥቅማጥቅም ፕሮግራሞች ለመሳተፍ ብቁ ሊሆኑ የሚችሉ ቤተሰቦች እንዴት ማመልከት ይችላሉ የሚለውን በሚመለከት መረጃ እዚህ ማግኘት ይችላሉ ወይም ለDHS ኢኮኖሚ ዋስትና አስተዳደር (ESA) የህዝብ ጥቅማጥቅሞች የጥሪ ማዕከል በ(202)727-5355 መደወል ይችላሉ። ለ TTY፣ እባክዎን ወደ (202)727-5355 ወይም 711 ይደውሉ። ለ TDD፣ እባክዎ ወደ (800) 537-7699 ይደውሉ።